ለሲሚንቶ ደንበኞች በሙሉ

 

ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በተሰጠን መመሪያ መሠረት ከሚያዚያ 28 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ለግል ቤት ገንቢዎች ብቻ የሲሚንቶ ሽያጭ ስለሚከናወን ከዚህ በታች ባለው ፕሮግራም መሠረት አስፈለጊውን መረጃዎች ማለትም የታደሰ የግንባታ ፈቃድየካርታ ኮፒ እና መታወቂያ ኮፒ ከአዲስ ማመልከቻ ደብዳቤ ጋር በመያዝ ግዥ መፈፀም የምትችሉ መሆኑን በማክበር እናሳውቃለን፡፡

 

ማሳሰቢያ

 

ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዚያ 5 ቀን 2013 ዓ/ም ድረስ በነበረው ፕሮግራም የተስተናገዳችሁ ደንበኞች በዚህኛው ፕሮግራም የማትስተናገዱ ሲሆን በቀጣይ በሚወጣው ፕሮግራም ላይ የምትስተናገዱ ይሆናል፡፡

 

ከተፈቀደለት ደንበኛ ውጭ ለመስተናገድ ሙከራ ሲያደርግ የተገኘ ደንበኛ በቀጣይ ምንም ዓይነት የሲሚንቶ ሽያጭ እንደማይከናወንለት በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

 

ደንበኞች የሲሚንቶ መግዣ ገንዘብ ባንክ ከማስገባታቸው በፊት የሚፈልጉትን የሲሚንቶ ዓይነትና መጠን በቅድሚያ ከሽያጭ ቡድን መረጃ ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡ የሽያጭ ክፍሉን ሳያማክሩ ወደ ዘርፉ አካውንት የሚደረገው የገንዘብ ማስገባት ተግባር ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ ይህን የሚያደርጉ ደንበኞች የማይስተናገዱ መሆኑን በጥብቅ እንገልጻለን፡፡             

 

ከሚያዚያ 28 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ለሲሚንቶ ተጠቃሚ ደንበኞች የወጣ የሽያጭ ፕሮግራም

 

1

የካ ክፍለ ከተማ እና ቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የግል ግንባታ የሚያካሂዱ - ከየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 እና 14 ወደ ለሚኩራ ክፍለ ከተማ የዞረ በመሆኑ የማይስተናገድ

ሐሙስ ሚያዚያ 28 ቀን 2013 ዓ/ም

የካ ክፍለ ከተማ በበር ቁጥር 1 እና ቂርቆስ ክፍለ ከተማ በበር ቁጥር 2

2

አዲስከተማ ክፍለ ከተማ እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የግል ግንባታ የሚያካሂዱ

አርብ ሚያዚያ 29 ቀን 2013 ዓ/ም

አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በበር ቁጥር 1 እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በበር ቁጥር 2

3

ቦሌ ክፍለ ከተማ እና ለሚኩራ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የግል ግንባታ የሚያካሂዱ

- ለሚኩራ ከቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08፣ 09፣ 10፣ 11 እና 15 - ከየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 እና 14

ቅዳሜ ሚያዚያ 30 ቀን 2013 ዓ/ም

ቦሌ ክፍለ ከተማ በበር ቁጥር 1 እና ለሚኩራ ክፍለ ከተማ በበር ቁጥር 2

4

ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ እና አራዳ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የግል ግንባታ የሚያካሂዱ

ሰኞ ግንቦት 02 ቀን 2013 ዓ/ም

ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በበር ቁጥር 1 እና አራዳ ክፍለ ከተማ በበር ቁጥር 2

5

ልደታ ክፍለ ከተማ እና ጉለሌ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የግል ግንባታ የሚያካሂዱ

ማክሰኞ ግንቦት 03 ቀን 2013 ዓ/ም

ልደታ ክፍለ ከተማ በበር ቁጥር 1 እና ጉለሌ ክፍለ ከተማ በበር ቁጥር 2

6

ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የግል ግንባታ የሚያካሂዱ

ረቡዕ ግንቦት 04 ቀን 2013 ዓ/ም

ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በበር ቁጥር 1