ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ

የሥራ መደቡ መጠሪያ:- ነገረ ፈጅ

ደረጃ:- 8

ደመወዝ: 6,062.00

የትምህርት ዝግጅት:- ከታወቀ የት/ርት ተቋም በህግ፣ ወይም በተመሳሳይ የትምህርት ዘርፍ 10ኛ ክፍል+2፣10ኛ ክፍል+3 አጠናቆ በቅደም ተከተል የመካከለኛ ምሥክር ወረቀት ደረጃ 2 ወይም ዲኘሎማ ያለው/ያላት የደረጃ IV ከፍተኛ ዲኘሎማ ያለው/ያላት

የሥራ ልምድ:- ከምረቃ በኋላ በሙያው መስክ 6/4/0 ዓመት የሰራ/ች   

ክህሎት:- አማርኛና ኦሮምኛ ቋንቋ የሚችል/የምትችል

የሰው ሀይል ብዛት:- 1

የሥራ ቦታ:- አ/አ

የሥራ ዘርፍ (ክፍል):- ዋናው መ/ቤት

ማሳሰቢያ

 • መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት (5) ተከታታይ የሥራ ቀናት በተጠየቀው መስፈርት መሠረት ያላችሁን የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃ እንዲሁም መታወቂያ ካርድ ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ እና ካሪኩለም ቪቴ ከማመልከቻ ጋር በመያዝ ከዚህ በታች በተጠቀሱት የምዝገባ ቦታዎች በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
 • በአካል ቀርበው መመዝገብ ለማይችሉ የክልል አመልካቾች የተጠቀሰው የመመዝገቢያ ጊዜ ገደብ ሳያልፍ የትምህርት ማስረጃ፣ የስራ ልምድና መታወቂያ ኮፒ፣ ካሪኩለም ቪቴ ከማመልከቻ ጋር በማያያዝ በፖስታ ሣጥን ቁጥር 3321 በመላክ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
 • የገቢ ግብር መከፈሉን የማያረጋግጥና ደመወዝ ያልተጠቀሰበት የሥራ ልምድ ማስረጃ ተቀባይነት የለውም፡፡
 • በሙያው ልምድ ያለው ይበረታታል፡፡
 • የአመልካች ዕድሜ ከ50 ዓመት መብለጥ የለበትም፡፡
 • ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ፡፡

የምዝገባ ቦታዎች

 • ደብረዘይት መንገድ በቅሎ ቤት ከጠመንጃ ያዥ ባንክ ፊት ለፊት በሚገኘው በኢትዮጵያ የንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት የሰው ሀብት አቅርቦትና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 506 በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
 • ለተጨማሪ መረጃ 0114-66-39-48 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
 • የፈተና ጊዜ፡- በውስጥ ማስታወቂያና በተሰጠው የስልክ አድራሻ ጥሪ ይደረጋል፡፡
 • የፈተና ቦታ፡- አዲስ አበባ

የመመዝገቢያ ሰዓት

 • ከሰኞ እስከ ሐሙስ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 10፡30 ሰዓት
 • ዓርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 5፡30 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 10፡30 ሰዓት
 • ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው፡፡

ስለ ኮርፖሬሽኑ ዝርዝር መረጃ ለማወቅ እና የሚወጡ የሥራ ማስታወቂያዎችን በቀላሉ ለማግኘት facebook.com/etbc.official፣ Telagram: t.me/etbcinfo እና ድረ-ገፅ www.etbc-ethiopia.com ይጎብኙ፡፡