ስለ እኛ የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን ባወጣው አዋጅ ቁጥር 916/2008 አንቀጽ 5 መሠረት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 369/2008 ታኅሳስ 12 ቀን 2008 ዓ/ም የተቋቋመ የፌዴራል መንግሥት የልማት ድርጅት ነው፡፡ ኮርፖሬሽኑ በተናጠል ሲንቀሳቀሱ የነበሩትን የኢትዮጵያ የእህል ንግድ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ ገበያ አክስዮን ማህበር እና የግዥ አገልግሎት ድርጅትን በማቀፍ በንግዱ ዘርፍ ከተሠማሩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ተጠቃሚነት ላይ በተመሠረተ መደጋገፍና መተባበር በመሥራት የንግድ ግብይት ሥርዓቱን የተረጋጋ፣ ዘመናዊ፣ አስተማማኝና ውጤታማ ለማድረግና ተወዳዳሪ ተቋም ሆኖ ለመገኘት የሚሠራ የመንግሥት የልማት ተቋም ነው፡፡
|
![]() |
የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በአገር ውስጥ የሚታየው የዘይት ምርት ዋጋ ንረትና አቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ በመንግሥት በተላለፈው ውሳኔ ከተገዛው ውስጥ የ5 ሚሊየን ሊትር የፓልም ዘይት ሥርጭት እያከናወነ ነው፡፡ ጅቡቲ ከሚገኘው ጎልደን...
ታህሣሥ 25/2015 ዓ.ም - ህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የምግብ ዘይት አንዲያገኝ በጅቡቲ ከሚገኘው ጎልደን አፍሪካ ካምፓኒ የ43 ሚሊዮን 37 ሺ 412 ሊትር የፓልም የምግብ ዘይት ግዢ መፈጸሙን የገንዘብ ሚኒስቴር አሰታውቋል፡፡ የግዢ...
የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽንን በቅርቡ ለተቀላቀሉ አዲስ ሰራተኞች የትውውቅ ስልጠና ታህሳስ 13 ቀን 2015 ዓ/ም ተካሄደ፡፡ ስልጠናውን ያዘጋጀው የኮርፖሬት የሰው ሃብት ልማትና ሥራ አፈጸጻም አመራር ቡድን ሲሆን የስልጠናው ዓላማ ለአዲስ...