|
አቶ አቻ ደምሴ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ስልክ፡ +25111 465 2436 ፋክስ፡ +25111 465 5428 |
ዋና ዋና ተግባራት የኮርፖሬሽኑን ሥራዎች ማቀድ፣ ማደራጀት፣ መምራት፣ ማስተባበርና መቆጣጠር፤ ኮርፖሬሽኑ ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚያደርጋቸው ግንኙነቶች፣ በሚያቀርባቸው ክሶችና በሚቀርቡበት ክሶች ኮርፖሬሽኑን ወክሎ መሥራት፤ ቦርዱን በማስፈቀድ ተጠሪ የሥራ ኃላፊዎችን መቅጠር፣ ተግባራቸውን መወሰን፣ ማሰናበት፤ በኮርፖሬሽኑ የውስጥ ደንብና አግባብ ባለው ህግ መሠረት ሌሎች ሠራተኞችን መቅጠር፣ መመደብ፣ ደመወዛቸውንና አበላቸውን መወሰን፣ ማሰናበት፡፡ |
||
![]() |
አቶ ቀጸላ ሸዋረጋ የኮርፖሬት ኦፕሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ስልክ፡ +25111 466 5037 ፋክስ፡ +25111 465 2792 |
ዋና ዋና ተግባራት የኮርፖሬሽኑን አጠቃላይ የኦፕሬሽን ሥራዎች ማቀድ፣ ማደራጀት፣ ማስተባበር፣ መምራት፣ መቆጣጠር፤ በሥሩ የሚገኙ የንግድ ዘርፎች አዘጋጅተው የሚያቀርቡትን የአጭር፤ የመካከለኛና የረዢም ጊዜ የሥራ ዕቅድና ፕሮግራም አጠቃልሎ ማዘጋጀት፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ማዋል፤ የወጪዎች የበጀት ጣሪያዎች መጠበቃቸውንና አጥጋቢ የሥራ ውጤት ማስገኘታቸውን ማረጋገጥ፤ ለዓለም ገበያ የሚቀርቡ የቡና፣ የእህል፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች በሚፈለገው መጠን፣ ዓይነትና የጥራት ደረጃ በወቅቱ ተገዝተው በክምችት መያዛቸውን ማረጋገጥ፡፡ |
||
|
አቶ ታሪኩ በራሱ የኢንሥኮ ኮርፖሬት ሰርቪስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ስልክ፡ +25111 466 3943 ፋክስ፡ +25111 465 2792 |
ዋና ዋና ተግባራት የኮርፖሬት ሰርቪስ ሥራዎችን ማቀድ፣ ማደራጀት፣ ማስተባበር፣ መምራትና መቆጣጠር፤ የፋይናንስ፣ የሰው ሀብት፣ የግዥና አቅርቦት ፖሊሲዎችን፣ መመሪያዎችንና ፕሮሲጀሮችን ማስተግበር፤ የኮርፖሬሽኑን የፋይናንስ አስተዳደር፣ የሰው ሀብት ሥራ አመራር፣ የግዥና ንብረት አስተዳደር ሥራዎችን የሚመለከቱ የፖሊሲ ሃሳቦችን ማመንጨት፣ ሲፈቀዱ አተገባበራቸውን መከታተል፤ የኮርፖሬሽኑ ሀብት በአግባቡ ሥራ ላይ መዋሉን መከታተል፡፡ |
||
|
ወ/ሮ አጸደ ገብረመስቀል የኮርፖሬት ህግ፣ ማኅበራዊ ጉዳዮችና የአሠራር ዘዴ ማሻሻያ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ስልክ፡ +25111 416 6435 ፋክስ፡ +25111 465 2792 |
ዋና ዋና ተግባራት የኮርፖሬት የህግ፣ የማህበራዊ ጉዳዮችና የአሠራር ማሻሻያ ሥራዎችን ማቀድ፣ ማደራጀት፣ ማስተባበር፣ መምራት፣ መቆጣጠር፤ የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በፀረ-ሙስና ፖሊሲዎች፣ ሕጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ላይ ግንዛቤ እንዲያገኙ ስልጠና መስጠት፤ የሥርዓተ-ጾታና ወጣቶች ጉዳይ በኮርፖሬሽኑ ስትራቴጂክ ሥራዎች ውስጥ ለማካተት የሚያስችል ጥናት፣ ስትራቴጂና መመሪያ መቅረጽ፣ ተግባራዊነቱንም መከታተል፤ ተቋማዊ ልማትን የሚያመጡ በምርጥ ተሞክሮ ላይ የተመሠረቱ አዳዲስ የአሠራር ማሻሻያ ዘዴዎችን በመቀመር ተፈጻሚ እንዲሆኑ ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣ ማስተባበር፡፡ |