Palm_Oil_Import.jpg

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በአገር ውስጥ የሚታየው የዘይት ምርት ዋጋ ንረትና አቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ በመንግሥት በተላለፈው ውሳኔ ከተገዛው ውስጥ  የ5 ሚሊየን ሊትር የፓልም ዘይት ሥርጭት እያከናወነ ነው፡፡

ጅቡቲ ከሚገኘው ጎልደን አፍሪካ የተባለ የምግብ ዘይት አምራች ኩባንያ በኮርፖሬሽኑ በኩል ተገዝቶ የቀረበው ይህ ምርት ኮርፖሬሽኑ በአጠቃላይ ውል ከተፈራረመበት 21.5 ሚሊየን ሊትር የዘይት ምርት ከታኅሣሥ 21 ቀን 2015 ጀምሮ በተካሄደው የመጀመሪያ ዙር የምርት ሥርጭት 2,389,660 ሚሊየን ሊትር ዘይት በኮርፖሬሽኑ የምርት ማከፋፈያ ማዕከላት አማካኝነት በባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ ጋምቤላ፣ ጅማ፣ ድሬዳዋ እና አዲስ አበባ ከተሞች ተሠራጭቷል፡፡

የዘይት ምርቱ መንግሥት ባወጣው የዋጋ ተመን መሠረት በሸማቾች የኅብረት ሥራ ማኅበራትና በተፈቀደላቸው አቅራቢዎች አማካኝነት ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር በተላለፈው ኮታ መሰረት ለኅብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ነው እየቀረበ ይገኛል፡፡ ቀሪው ዘይት በተከታታይ ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት የሚሰራጭ ይሆናል፡፡

በሌላም በኩል ኮርፖሬሽኑ የአገር ውስጥ ገበያን በማረጋጋት ተልዕኮው በዓሉን በማስመልከት ነጭ ጤፍ እና የዳቦ ዱቄት ለመንግሥት ሠራተኞች፣ እና ለልዩ ልዩ ተቋማት  በዝቅተኛ  ዋጋ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡