የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሚያከናውናቸው የምርት የግብይት ሥራዎች ለማሳለጥ የመያገለገሎ ተጨማሪ አራት ከባድ ተሽከረካሪዎች ግዢ አከናወነ፡፡ የተሸከርካሪ ርክክቡ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት በተከናወነበት ወቅት አንደተገለጸው የተገዙት ተሸከርካሪዎች እያንዳንዳቸው 50 ኩንታል፣ በድምሩ 200 ኩንታል የመጫን አቅም ያላቸው ሲሆን በአጠቃላይ ከ11.4 ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጎባቸው ኢትዮ ኒፖን ከተባለው ኩባንያ የተገዙ ናቸው፡፡