Vegetable_Oil.jpg

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በአገራችን ያለውን መሠረታዊ የምግብ ፍጆታ ምርቶች አቅርቦት እጥረትና የዋጋ ንረትን ለመቋቋም የተለያዩ የፍጆታ ምርቶችን በማከፋፈል ገበያውን ማረጋጋት እና የሃገር ውስጥ አምራቾችን ማበረታታት ከተሰጡት ተልዕኮዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡

በመሆኑም ኮርፖሬሽኑ ከፊቤላ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ.ማህበር የ26 ሺህ ሊትር የሱፍ የምግብ ዘይት ግዢ በመፈጸም ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ ውስጥ 6 ሺህ ሊትር በኮርፖሬሽኑ የአትክልትና ፍራፍሬ ሱቆች በኩል ለህብረተሰቡ ፍጆታ እንዲውል የተደረገ ሲሆን ቀሪው 20 ሺህ ሊትር ደግሞ በቅርቡ የሚሰራጭ ይሆናል፡፡ ባለ አምስት ሊትር የሱፍ የምግብ ዘይቱ በ930 ብር በአዲስ አበባ እና በክልሎች እየተሸጠ ሲሆን ይህም ገበያ ላይ ካለው ዋጋ ጋር ሲነጻጸር 13 በመቶ ያህል ቅናሽ ያለው ነው፡፡