DSC_01.JPG

ግንቦት 12 ቀን 2015 ዓም በቀድሞው ግሎባል በአሁኑ የኢትዮጵያ ሆቴል በተካሄደው የምስጋና ዕውቅና መርሃ ግብር ኮርፖሬሽኑ በ2015 ዓ/ም በተካሄደው 8ኛው የካይዘን ዓመታዊ የሽልማት ውድድር በካይዘን ትግበራና ውጤታማነት በአገልግሎት ዘርፍ 3ኛ ደረጃ ተሸላሚ፤ አቢሲኒያ የጥራት ሽልማት ድርጅት ባካሄደው ዓመታዊ የጥራት ውድድር በአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ ሥራ ዘርፍ ዘመናዊ አሠራር በመዘርጋት፣ የላቀና ተጨባጭ ዕድገት በማስመዝገብ እንዲሁም መልካም ስምን ጠብቆ ለአመታት በትጋት በመዝለቅ የወርቅ ዋንጫ ተሸላሚ ላደረጉ ሠራተኞችና አመራሮች የምስክር ወረቀትና ሽልማት ተበርክቷል፡፡

የኮርፖሬሽኑ የህግ፣ ማህበራዊ ጉዳዮችና አሠራር ማሻሻያ ም/ዋ/ሥ/አስፈጻሚ ተወካይ አቶ ይርጋሸዋ ተሾመ በመርኃ ግብሩ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ኢንሥኮ ካይዘንን በተቋም ደረጃ ከተገበረበት ጊዜ አንስቶ አሠራሩን ከፍልስፍና ባለፈ በሁሉም ሠራተኛ ዘንድ ሰርጾ እንደ አንድ መሳሪያ ጥቅም ላይ መዋል መጀመሩን አስረድተው በዚህም በተጨማሪ ገቢ፣ የሥራ ቦታና ወጪ ቅነሳ አበረታች ውጤቶች መገኘታቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ኮርፖሬሽኑ በካይዘን ትግበራ ለደረሰበት ስኬት ብሎም በአገልግሎት ዘርፍ በአገር አቀፍ ደረጃ ላገኘው ዕውቅና የኢትዮጵያ ካይዘን ልቀት ማዕከል ከአመራሩ ጀምሮ ባለሙያዎችን በማሠልጠንና አማካሪዎችን በመመደብ ያደረገው ክትትል ዓይነተኛ ሚና መጫውቱን አውስተው፤ በቀጣይም ሁሉም አካላት የተገኙ ውጤቶችን በሁሉም ዘርፍ፣ የሥራ ክፍሎችና ማዕከላት ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በተመሣሣይም የኮርፖሬሽኑ የአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ ሥራ ዘርፍ በአቢሲኒያ የጥራት ሽልማት ውድድር ላይ ምርትን ለበርካታ ዓመታት ለህብረተሰቡ በጥራት በማቅረብ፣ አሠራን በማዘመን፣ በታማኝነትና በሌሎችም የላቁ አሠራሮች በውጤታማ አመራር ሰጪነትና በሠራተኛው ትጉህ እቅስቃሴ ለወርቅ ዋንጫ፣ ሜዳሊያና ኒሻን ሽልማት በመብቃቱ የተሰማቸውን ደስታና በመግለጽ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የኮርፖሬሽኑ ተልዕኮ ህብረተሰብን ማገልገል ከመሆኑ አኳያ የተገኘው ሽልማትና ዕውቅና ይህን ዓላማ ለማሳካት እንደ መስፈንጠሪያ ሆኖ ሊያገለግል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በመድረኩ ላይ ኮርፖሬሽኑ ተሸላሚ በሆነባቸው መስኮች የተከናወኑ አበይት ተግባራትና የሽልማቶቹ የተገኙባቸውን ሂደቶች የተመለከቱ መረጃዎች የቀረቡ ሲሆን፤ ለካይዘን የልቀት ማዕከል እና የአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ ሥራ ዘርፍ ላገኘው ዕውቅናና ሽልማት ስትራቴጂካዊ አቅጣጫና አመራር በመስጠት አስተዋጽዖ ላበረከቱ የንግድ ሥራ ዘርፎችና ለኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የምስጋና ሽልማቶች ተበርክተዋል፡፡

በመርኃ ግብሩ ማጠቃለያ ላይ የኮርፖሬሽና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አቻ ደምሴ የተገኘው ውጤት የተቋሙን ዓላማ ተልዕኮ ከግብ ለማድረስ የሚተጉ አመራና ሠራተኞች ውጤት መሆኑን ገልጸው፤ የተገኘው ውጤት በቀጣይ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል አመላካች መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የደንበኞችን እርካታ ጥራቱ በጠበቀ አገልግሎትና ምርት አቅርቦት እንዲሁም ተደራሽነት ማጎልበት እንደሚገባ፤ ለዚህም የፈጸሚን የመፈጸም አቅም ለማጎልበት ሥራን የያሳልጡ፣ ወጪ ቆጣቢ፣ ብክነትን የሚከላከሉና የተሻሻሉ የሥራ ማሳለጫ መሣሪያዎችን በሥፋት ሥራ ላይ የማዋሉ ተግባር ሊጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

 ተጨማሪ ምስሎችን እዚህ ማየት ይችላሉ፡፡

 

የማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችችን በመቀላቀልና የምርትና አገልግሎት መረጃዎችን በቀላሉና በፍጥነት ያግኙ!
ድረገጽ፡- https://www.etbc-ethiopia.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/etbcofficial
ቴሌግራም፡- https://t.me/etbcinfo
ዜና ኢንሥኮ አንድሮይድ መተግበሪያ፡- https://t.ly/DiXR
ዩትዩብ ቻነል፡- https://www.youtube.com/@etbcinfocom4858
አስተያየትዎን በኢሜይል አድራሻችን This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ያድርሱን፡፡
ኮርፖሬት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት