የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በዋናነት የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችን፣ መሠረታዊ ሸቀጦችን ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር በተወዳዳሪ ዋጋ በመግዛት ለአርሶ አደሩና አምራቹ የገበያ ዕድል ለመፍጠር፤ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችን እንዲሁም መሠረታዊ ሸቀጦችን ለሸማቹ ማኅበረሰብ ለመንግሥትና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማትና ለዱቄት ፋብሪካዎች በመሸጥ ገበያን ለማረጋጋት፤ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ላልሆኑ ተቋማት የውክልና ግዥ ለማካሄድና በግዥ ዙርያ የማማከርና የሥልጠና አገልግሎት ለመስጠት፤ የሀገራችንን ቡና፣ የቅባት እህል፣ ጥራጥሬ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ለውጭ ገበያ በመሸጥ የውጭ ምንዛሪን ለሀገራችን ለማስገኘት የተቋቋመ የፌደራል የመንግሥት የልማት ድርጅት ነው፡፡

 

የንግድና አገልግሎት ዘርፎች

 

እህልና ቡና 
 
የኢንሥኮ የእህልና ቡና ንግድ ሥራዎች በዋነኝነት የተመረጡ የእህል ምርቶችን ቅባትና እና ጥራጥሬ እህሎች፤ እንዲሁም ቡናን ከአገር ውስጥ አምራቾች በመግዛት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ በማቅረብ አርሶ አደሩ የእህል ማምረት ፍላጎቱን በማሳደግ ገበያ መፍጠር ߹ ለህብረተሰቡንም የእህል ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ግብይቱን የተረጋጋ ያደርጋል፡፡ በዚህም ለሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት ለልዩ ልዩ ተቋማት የግብርና ምርቶች አቅርቦት ይካሄዳል፡፡ 
ለሀገር ውስጥ ገበያ ማረጋጊያ የሚውሉ የምግብ እህሎች 
• ጤፍ 
• የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ስንዴ 
• በቆሎና ገብስ
ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ተገዝተው ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የግብርና ምርቶች
- የታጠበ ቡና (የሲዳማ፣ የይርጋጨፌ፣ የነቀምት፣ የሊሙ)
- ያልታጠበ ቡና (የሐረር፣ የሲዳማ፣ የጅማ፣ የቴፒ፣ የነቀምት)
- የቅባት እህሎች (ነጭ የወለጋና የሁመራ ሰሊጥ፣ ኑግ፣ ተልባ)
- ጥራጥሬ (ነጭና ቀይ ቦሎቄ፣ ባቄላ፣ አኩሪ አተር፣ ማሾ፣ ሽምብራ)
አቅራቢዎች
• የአርሶ አደር ኅብረት ሥራ ማኅበራት 
• የመንግሥትና የግል አምራቾች 
የወጪ ንግድ መዳረሻዎች
ቻይና፣ ፈረንሣይ፣ ኮሪያ፣ እስራኤል፣ አሜሪካ፣ ጅቡቲ፣ ቤልጅየም፣ ዱባይ
የግብይት ቦታዎች
በኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያቤት የውጭ ስንዴ እና ሌሎች የግብርና ምርቶች ሽያጭ የሚከናወን ሲሆን በሁሉም ክልሎች ባሉ 122 ክልሎች ግብይት ማዕከላትና ጣቢያዎች የውጭ ስንዴ እና ሌሎች የግብርና ምርቶች ግብይት ይከናወናል፡፡
ለመረጃ
ስልክ: +251114167884/68
ፋክስ: +251114704373

አትክልትና ፍራፍሬ
 
የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በአትክልትና ፍራፍሬ ንግዱ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን ከአገር ውስጥ አምራቾች በመግዛት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ  የሚያቀርብ ሲሆን የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች የሆኑ መሰረታዊ  ሸቀጦችን አቅርቦትን በማሳደግ ገበያን በቀጥታ  የማረጋጋት እንዲሁም ለሀገራችን ስነ-ምህዳር የሚስማማሙ የተመረጡ የአትክልት ዘሮችን ከወጭ ሀገር አስመጥቶ አምራቾችን ተጠቃሚ የማድረግ ሥራዎችን ያከናውናል፡፡ በተጨማሪም ልዩ ልዩ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን ለውጭ ገበያ ያቀርባል፡፡ 
የምርት ዓይነቶች
- ብርቱካን፣ ሙዝ፣ ማንጎ፣ አናናስ፣ ካሮት፣ ሽንኩርት፣ ድንች፣ ቲማቲም፣ ስኳር ድንች፣ መንደሪን፣ ኮምጣጤ፣ 
- የቲማቲም ድልህ፣ የቲማቲም ጭማቂ፣ የብርቱካን ማርማላት፣ ፓስታና ማካሮኒ፣ ሩዝ
- የተለያዩ የአትክልት ዘሮች
- ዱቄት፣ ስኳርና የምግብ ዘይት
አቅራቢዎች
አትክልትና ፍራፍሬ አምራች ገበሬዎች፣ እርሻ ልማቶች
ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶች
ማንጎ፣ አቮካዶ፣ ቲማቲም፣ ሙዝ፣ ብርቱካን፣ ድንች
የወጪ ንግድ መዳረሻዎች
ጅቡቲ፣ ሶማሊላንድ
የሽያጭ/ማከፋፈያ መደብሮች
- በአዲስ አበባ የሚገኙ የችርቻሮ መሸጫ መደብሮች
- በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የሽያጭ ኮንቴነሮች የችርቻሮ ሽያጭ ይካሄዳል
   
የማከፋፈያ መደብሮች 
- ፒያሳ - አትክልት ተራ ጎን
- አፍንጮ በር - ስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ አምስተኛ በር አካባቢ
- ቄራ - በኢንሥኮ የአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ ዘርፍ ዋና መሥሪያ ቤት 
በክልሎች
-በሁሉም ክልሎች በሚገኙ 105 አትክልትና ፍራፍሬ ማከፋፈያ ማዕከላትና የመሸጫ ሱቆች ሽያጭ ይካሄዳል 
ለመረጃ
ስልክ: +251114164288፣ +251114160338 

የፍጆታ ዕቃዎች 
 
ኢንሥኮ በፍጆታ ዕቃዎች ንግድ ሥራው ምርቶችን ከውስጥና ከውጭ አምራቾች በማቅረብ የገበያ ዋጋን የማረጋጋትና ለሸማቹን በተመጣጣኝ ዋጋ የምርት አቅርቦትን ለማረጋገጥ ይሠራል፡፡ የንግድ ሥርዓቱ የምርት ሰንሰለትም ያጠረ እንዲሆን በማድረግ  ጥራቱን የጠበቀ ምርት በአስተማማኝነት በሸማቾች ማህበራት፣ በሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣  ካፌዎችና በቸርቻሪዎች በኩል በቀጥታ ለሸማቹ እንዲደርሱ ይደርጋል፡፡
የምርት ዓይነቶች
- መሠረታዊ የምግብ ሸቀጦች (ዘይት፣ ስኳር፣ የስንዴ ዱቄት)
- የታሸጉ ምግቦች
- የተለያዩ ለስላሳ መጠጦች 
- የቤትና የግል ንጽህና መጠበቂያዎች 
- መቆያና ጣፋጭ ምግቦች 
- የጽህፈት መሳሪያዎች በተመጣጣኝ ዋጋ በቸርቻሪዎች አማካይነት ለተጠቃሚዎች በመሸጥ  የፍጆታ ሸቀጦች ዋጋን ማረጋጋት ነው፡፡
የፍጆታ ሸቀጦች ግብይት ማዕከላት
በአዲስ አበባ
- ቃሊቲ - ደብረ ዘይት መንገድ ቆርኪ ፋብሪካ ፊትለፊት 
- መገናኛ - ኒያላ ሞተርስ አጠገብ 
- መርካቶ - የቀድሞው ጅንአድ ግቢ ውስጥ 
          
በክልሎች
- በሀዋሳ - ሃዋሳ ግብርናኮሌጅ በስተጀርባ 
- በሻሸመኔ - ከኢትዮ ቴሌኮም ፊትለፊት 
- በደሴ - ደሴ የአውቶቡስ ጣቢያ/ከአምባሰል ንግድ ስራ ጎን
- ባህርዳር - ፓፒረስ ሆቴል
ለመረጃ
ስልክ: +251114705454 
+251114716132 
+251114717834 

የግዢና ማማከር አገልግሎት
 
ኢንሥኮ በዋናነት በውክልና ግዥ የመፈጸምና በግዥ ዙርያ የማማከርና የሥልጠና አገልግሎቶችን መንግሥታዊና መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ይሰጣል፡፡ የግዥና የማማከር አገልግሎት በመደበኛ ግዥ ለጨረታ አጽዳቂ ኮሚቴ በሚረዱ አሠራሮች፣ በግዥና አቅርቦት ማኔጅመንት፣ በኮንትራት ማቴሪያል ማኔጅመንት እንዲሁም በገቢና ወጪ ንግድ ፕሮሲጀር ስራዎች የሚሰጣቸው ስልጠናዎች በአንድም ሆነ በሌላ በኩል በአገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄዱ ዋና ዋና ሰፋፊና ከፍተኛ የቴክኒክ እውቀት የሚሹ ግዥዎችን እውን በማድረግ የግዥ ሂደቱን ውጤታማ በማድረግ እውቀትን በማሸጋገር በመንግሥት ተቋማት ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን በማስወገድ የፕሮጀክቶች አፈጻጸምን በማቀላጠፍና በሌሎችም መስኮች ችግርን ለመፍታትና ሥራን ለማሳለጥ ሰፊ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡
ለመረጃ
ስልክ: +251 11 440 3613
ፋክስ: +251 11 440 3579
ተጓዳኝ አገልግሎቶች
 
ከመደበኛ የንግድ ሥራዎቻችን ባሻገር ለውጭ ተጠቃሚዎች በዘመናዊ የማበጠሪያ ማሽኖች ቅባትና ጥራጥሬ የማበጠር፣ በአዲስ አበባና በክልሎች የመጋዘን ኪራይ፣ የእህል እጥነትና የጭነት ማጓጓዝ አገልግሎት እንሠጣለን፡፡
ለመረጃ
ስልክ: +251114420594 (የጭነት ማጓጓዝ ) , +251114402754 (ቅባትና ጥራጥሬ ማበጠር፣ የእህል እጥነት)