ስለ እኛ የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን ባወጣው አዋጅ ቁጥር 916/2008 አንቀጽ 5 መሠረት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 369/2008 ታኅሳስ 12 ቀን 2008 ዓ/ም የተቋቋመ የፌዴራል መንግሥት የልማት ድርጅት ነው፡፡ ኮርፖሬሽኑ በተናጠል ሲንቀሳቀሱ የነበሩትን የኢትዮጵያ የእህል ንግድ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ ገበያ አክስዮን ማህበር እና የግዥ አገልግሎት ድርጅትን በማቀፍ በንግዱ ዘርፍ ከተሠማሩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ተጠቃሚነት ላይ በተመሠረተ መደጋገፍና መተባበር በመሥራት የንግድ ግብይት ሥርዓቱን የተረጋጋ፣ ዘመናዊ፣ አስተማማኝና ውጤታማ ለማድረግና ተወዳዳሪ ተቋም ሆኖ ለመገኘት የሚሠራ የመንግሥት የልማት ተቋም ነው፡፡
|
![]() |
በሥራ አካባቢ ደኅንነትና ጤንነት ላይ ያተኮረ የሁለት ቀናት ሥልጠና ከኮርፖሬሽኑ ዋና መሥሪያ ቤትና ከንግድ ሥራ ዘርፎች ለተውጣጡና በተለያዩ መደቦች ላይ ለሚሠሩ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች ከግንቦት 9-12/2014 ዓ/ም በሁለት ዙር በዋናው...
በኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤትና በአራቱም ዘርፎች የካይዘን እጩ አማካሪዎች የትግበራ ግምገማ ግንቦት 9/2014 ዓ.ም ተካሄደ፡፡ የግምገማ መድረኩን የመሩት አቶ ትእዛዙ ኃ/ ጊዮርጊስ የኮርፖሬት አሰራር ዘዴና የአገልግሎት ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና...
የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በከፍተኛ ሁኔታ የናረውን የዘይት ዋጋ ለማረጋጋት ተጨማሪ የ 10 ሚሊየን ሊትር ፓልም የምግብ ዘይት ግዥ ለመፈጸም ውል ገብቷል፡፡ በቅርቡም ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገባና እንደሚሰራጭ ተገልጿል፡፡ ኮርፖሬሽኑ...